📝 የፈተና አሰራር ሚስጥር 📝
💬 ማስታወሻ ፦
🧲በቅድሚያ ብዙ የሚፈልጉ ሰዎች
ስላሉ እባክዎ ሼር ያድርጉት ⤴️
📚 ስለ ፈተና አሰራር የምናወራው አንድ ተማሪ ለፈተናው በሚገባ ዝግጅት አድርጓል የሚለውን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል። ታድያ አንድ ተማሪ ለፈተና ተገቢውን ዝግጅት አድርጎ ፈተና ላይ ስለ ተቀመጠ ብቻ የሚፈልገውን ውጤት ያስመዘግባል ማለት አይደለም ለዚህ አንዱ ምስክር እኔ ነኝ። ምን ለማለት ፈልጌ መሳላችሁ ፈተና በምንሰራበት ጊዜ የሚከተሉተን ነገሮች መከተል አለብን ፦
✅ 1ኛ፦ ፈተናውን አሰራዋለሁ የሚል ወኔ (Courage) ሊኖረን ይገበል። becoz ምንም ያክል ብናነብ ፈተና ገብተን የምንፈራ ከሆነ አደለም የማናቀውን የምናቀውን ጥያቄ ሁሉ ሊጠፋብን ይችላል ስለዚህ በራስ መተማመን ሊኖረን ይገባል ማለቴ ምችለውን ያክል አንብቢያለሁ ስለዚህ ፈጣሪ ይረዳኛል አሰራዋለሁ የሚል ወኔ💪 ያስፈልጋል።
❇️2ተኛ ፈተናውን ስንሰራ ማስተዋል አለብን። ይህ ምን ማለት ነው ለምሳሌ አንዳንድ ጥያቄዎች ቀላል ሲመስሉን አራቱንም አማራጮች ሳናይ Choice A ወይንም B ን ብቻ አይተን ልንሸወድ እንችላለን ምክንያቱም ሌላ የተሻለ መልስ ሊኖር ይችላል ስለዚህ እንደ English,civics Biology, History ነክ ጥያቄዎችን ስንሰራ ሁሉንም አማራጮች ትክክል ያልሆኑትን እና የሆኑትን የ✖️አና ✔️ምልክት እያደረግን ብንሰራ ጥሩ ነው እኔ በዚ ብዙ ጊዜ ተሸውጄ ስለማቅ ነው።
✳️ 3ተኛ ሰዓታችንን ባግባቡ መጠቀም በፈተና ጊዜ ከ ጥያቄው በተጨማሪ ሌላኛው ፈተና ሰዓት ነው so ሰዓታችንን ባግባቡ መጠቀም አለብን ማለት ነው ከቻላቹ በሆነ ጋፕ ፈታኙን ሰዓት በመጠየቅ ስንት ሰዓት እንደቀረን ማወቅ እንችላለን።ፈተናችንን on time ለመጨረስ የሚያስፈልጉ የተውሰኑትን ነጥቦች ልጥቀስ፦
⭕️ ፈጠን ብለን ፈተናችንን ለመስራት አንሞክር ፤ አንድ ጥያቄ ላይ አረጋግጣለሁ በማለት አለመተኛት ፤ በፍጥነት እየሞላን መሄድ ።
✏️ እንግሊዝኛ አይነት ፈተናውችን ስንሰራ reading comprehension ማለትም passage አንብበን የምንሰራቸው ጥያቄዎች ሰዓት ስለሚያስፈልጋቸው በመጨረሻ ብንሰራቸው ሰዓት የመቆጠብ እድላችን ሰፊ ነው ፦
🟥 የ calculation ጥያቄዎችን እንደ Maths ad Physics ስንሰራ ደግሞ እስክርቢቶ ወይንም እርሳስ ከወረቀታችን ጋር ከማገናኘታችን በፊት ጥያቄውን መረዳታችንን ማረጋገጥ አለብን becoz ከንቱ ላንሰራው ሁላ ጊዚያችንን ልንወስድ እንችላለን።
1⃣ መሰረታዊ መርሆችን (Fundamental Rules) መረዳት።
2⃣ ቁልፍ መረጃን(key information ) መለየት::
3⃣ ችግሩን (problem) በጥንቃቄ መገንዘብ እና አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች እና የሚጠየቁትን ያደምቁ (ምልክት) ወይም ያስተውሉ
4⃣ ንድፎችን መተጠቀም (diagram) ፡- • ለፊዚክስ ችግሮች ዲያግራም መሳል ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለማየት እና አቅጣጫዎችን ወዘተ ለመለየት ይረዳል
አዚ ጋ መጨመር ምፈልገው ደግሞ የከበደንን ጥያቄ ሲገዛገዙ መዋል ሳይሆን አንዱን ሞልተን ሰዓት ካለን ተመልሰን ማየቱ የተሻለ ነው።
❇️ 4ተኛ፦ሌላኛው ወሳኝ ነጥብ መፈተኛ ቦታ ቢቻል ቀደም ብለን ብንገኝ ጥሩ ነው ካልሆነ በትክክለኛው ሰዓት መገኘት አለብን ምክያቱም ካረፈድን ጭንቀት ውስጥ ልንገባ እንችላለን::
🖍👨💻እንግዲህ ካለኝ ልምድ በመነሳት ይህንን
ፃፍኩላችሁ ...✍
0 Comments