ውጤታማ የጥናት ዘዴዎች ለተማሪዎች

 

  ውጤታማ የጥናት ዘዴዎች ለተማሪዎች

⭐በትምህርት ስኬታማ መሆን የሚወሰነው እኛ ለጥናት በምንሰጠው ጊዜ ርዝመት ሳይሆን በምንጠቀመው ዘዴ ይወሰናል። ነገር ግን ብዙ ተማሪዎች ይህንን ባለመረዳት ውጤታማ በማያደርግ የጥናት መንገድ ሲጓዙ እናስተውላለን። ዛሬ በዚህ ሱሪያ በጣም የሚጠቅማችሁና ካላቹበት ደረጃ ከፍ ስለሚያደርጉዋቹ ዘዴዎችን እናያለን።እነዚህ ዘዴዎች  የአጠናን መንገዳችሁን እንደሚያስተካክሉላቹ አትጠራጠሩ።

1.የምንረዳበትን style ማወቅ

✔ሁሉም ተማሪ ነገሮችን በተመሳሳይ መንገድ አይረዱም ምክንያቱም እያንዳንዳችን የራሳችን የሆነ ነገሮች የምንረዳበት መንገዶች አሉ። እንትና ስለተረዳና ስለገባው አንተ ላይም ይሰራል ማለት አይደለም አንተ/ቺ የገባቹ መንገድ ለሌላውም ይገባዋል ማለት እንዳልሆነ መረዳት አለብን ። ለዚህም ነው በመጀመሪያ ደረጃ የራሳችንን style ማወቅ ያለብን።


✔ብዙ አይነት መንገዶች ሲኖሩ ከነሱ ጥቂቶችን የምናይ ይሆናል


1. Visual Learner ( ነገሮችን በማየት የሚረዱ)👀

  e.g diagram,chart and color coding...

2. Auditory Learner (ነገሮችን በመስማት የሚረዱ)👂

  e.g  lectures

3. Kineshetic Learner ( ነገሮችን በተግባር በመስራት የሚረዱ)🙌

  e.g  labe experement


2. Active Learning🧠



✔አንድን ነገር ደግመን ደጋግመን ማንበብ የውጤታችን መቀነስ ዋነኛ ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች አንዱ ነው። ብዙ ምሁራን እንደሚገልፁት ነገሮችን ይበልጥ ለመረዳትና ለማስታወስ Active Learning እንደሚረዳ ይናገራሉ።

✔በ Active Learning ውስጥ ከሚመደቡት መካከል ጥቂቶችን እንመልከት


1. Summarize (ያነበብነውን ነገር በራሳችን ቃል መልሰን መፃፍ)✍

2. Teach (ከንባብ መልስ ሌሎችን ማስረዳት/ማስተማር)3. Use Flashcard (የራሳችሁን  flashcard ማዘጋጀት ወይም መተግበሪያዎችን መጠቀም  Anki ወይም quizlet)

4. Practice Retrieval (የፃፋችሁትን ወይም ያነበባችሁትን ሳታዩ ራሳችሁን መፈተን)

✔እነዚህን በመጠቀም⭐ 1. የማስታወስ አቅማችሁን ታሳድጋላቹ
                                 ⭐  2. ነገሮችን በቀላሉ ትረዳላቹ


3. The Pomodoro Technique ⏰


✔የጥናታቹን ውጤታማነት ከሚገድሉ ዋነኛ ምክንያቶች መካከል አንደኛው distraction ወይም ትኩረት የሚረብሹ ነገሮች ናቸው።  የ pomodoro ዘዴ ደግሞ ነገሮች ላይ ትኩረት እንድታረጉ  ከሚረዳቹ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

🤔እንዴት እንጠቀም?


1. ለ 25 ደቂቃ Alarm ሙሉና በትኩረት ጥናታችሁን ጀምሩ

2. 25 ደቂቃው እንዳለቀ ለ 5 ደቂቃ እረፍት አድርጉ

3. ለ 4 ጊዜ ይህን ከደጋገማቹ በኋላ ከ 15 - 30 ደቂቃ ዕረፍት ውሰዱ

🧠ይህም ዘዴ አዕምሮዋቹ ንቁ ሆኖ እንዲ ቆይ ይረዳቹሃል

4. Space Reptation ♻️


✔ሰግጦ ማንበብ ለ short term ሊጠቅም ይችላል ነገር ግን  በጊዜ ሂደት ወዲያውኑ መረሳቱ የማይቀር ነው። ይህንንም ለማስቀረት space repetition መጠቀም ይረዳል

♻️ስናጠቃል space repetition  ያነበብነውን ነገር  በጊዜ ሂደት ክለሳ የምናደርግበት ዘዴ ነው። ይህም ያነበብነው ነገር ከኛ ጋር ለረጅም ጊዜ እንዲ ቆይ ያደርግልናል። ለዚህም እንዲረዳቹ Anki መተግበሪያን መጠቀም ትችላላቹ።

👉የምትከልሱበት interval ካነበባቹ ከ1 ቀን በኃላ  ከ 3 ቀን በኃላ ከ 1 ሳምንት በኃላ  ከ 1 ወር በኃላ ...

5.  የጥናት ሰሌዳ (schedule)  ማዘጋጀት📋

✔የተስተካከለና አመቺ የጥናት ሰሌዳ ማዘጋጀት ለስኬታማ የጥናት ዘዴ  ጠቃሚ ነው። ይህንንም ደግሞ ብዙዎች ተጠቅመው አስመስክረዋል።

🤔እንዴት ላዘጋጅ?

1. የሚከብዳሁን subject አስቀድሙ

2. ለ የ subject  ጊዜ ከፋፍሉ ( ለ 1 subject ከ 1 - 2 ሰዓት መጠቀም)

3. ለድንገተኛ  የሚወን ጊዜ ማዘጋጀት


💡ደግሞ እንዳትዘነጉ "consistency is key"

6. የ ማጥኛ ቦታ ማዘጋጀት🏫


✔በዙሪያቹ ያሉ ነገሮች በጥናት ሂደታቹ ላይ ትልቅ ተፅእሮ አላቸው። ለዚህም ነው የጥናት ቦታችሁን ስትመርጡ ማሰብ ያለባቹ። የተወሰኑ tip ጣል እናድርግላቹ

1. ፀጥታ ያለበትና ሰው የማይበዛበት ቦታ

2. noise canceling ተጠቀሙ ( head phone)

7 .  ራስን መፈተን♨️


ራስን መፈተን በጣም powerful እና አመርቂ ውጤት እንድታገኙ የሚረዳቹ ምርጡ ዘዴ ነው።

🤔እንዴት ራሴን ልፈትን?

1. ያለፈ ዓመት ጥያቄ መስራት

2. የራሳችሁን quize ማዘጋጀት  (AI ተጠቀሙ)

3. የጥናት group በመፍጠር እርስ በእርስ መጠያየቅ)

✔ይህን ስታደርጉ⭐ 1 . የተሳሳታችሁትን ለማረም ይረዳቹሃል
                          ⭐ 2. ደካማ የሆናቹበትን area እንድታስተካክሉ ይረዳቹሃል

8. በቂ ዕረፍት ማድረግ💤


✔አዕምሮዋችን እራሱን ለማደስ በቂ የሆነ ዕረፍት ያስፈልገዋል። በቂ እረፍት አለማድረግ አዕምሮዋችን እንዲደክም ያደርገዋል።

⏰በቀ1ን ከ 7 - 9 ሰዓት መተኛት

 

9. የ Feyman ዘዴን መጠቀም

🧠አንድን Concept እንድትረዱ የሚረዳቹ ዘዴ ነው።

1. ያነበባችሁትን ለሌላ ሰው ማስረዳት

2. ስታስረዱ የከበዳቹን ነገር መልሳቹ መከለስ

10. ራስን መሸለም🎁


✔ጥናት አጓጊ እንዲሆን ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል አንደኛው ሲሆን አሪፍ ውጤት እንድናስመዘግብ ይረዳናል።
- በመጀመሪያ እቅድ አዘጋጁ ( ዛሬ Biology Unit 1 አነባለሁ)
- ካሳካችሁ በኃላ ራሳችሁን ሸልሙ ( ደስ የሚላችሁን ነገር አድርጉ)

Post a Comment

0 Comments